About መረጃ
Seeing is believing Hearing is Everything
ማየት ማመን ነው መስማት አለም ነው
Expert Healthcare
ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት
Expert doctors
Comfortable facilities
Quality service
OUR PATIENTS SAY
ከታካሚዎቻችን አንደበት
ቃላቶች አጠሩኝዶፍ ቢወርድ አልሰማ ምድር ቢደረመስ
ክፋት ሀይል አውጥቶ ሀሰት ቢልከሰከስ
ተዋት ይቺ አትሰማም ቢሉኝ ቢያንቋሽሹ
ርካሽ የማትረባ ብለው ቢፈርዱብኝ በኔ ላይ ቢዋሹ
ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ቢታወጅ በዓለም ላይ
ስሜ በሜጋፎን ቢለፈለፍ በሰማይ
ሀይማኖት ቢሰብክ ህግ ቢያናግሩኝ
ቅጥ ያጣሁ ልጅ ነበርኩ ምኑም የማይገባኝ
በአንተው ብሩክ እጆች ይሄው ተፈውሼ
ድካምክን ለመግለጽ ቃላቶች ፈልጌ መጥኜ ደቁሼ
ርቄ ባልሄድም ይህንን ጫጭሬ እጅ ነስቻለው ደስታን ተንተርሼ።
“ መስማት ዓለም ነው!” በዚህ አለም ላይ ሰው ብሩህ እና ደስተኛ፤
በተስፋ የተሞላ ህይወት ለመኖር ጤና አስፈላጊ ነው። በህይወቴ የነበረው
ጎዶሎ ማንነቴን አላህ ሰበቡን ፈቅዶልኝ በተባረኩ በዶ/ር ኢስሀቅ በድሪ
እጆች ድኜ አልሀምዱሊላህ ለአሁኑ ማንነቴ በቃሁ!
ለስራህ የተሳካ ውጤትን፧ ጤናን፧ እድሜን እየተመኘሁ
ዶ/ር ኢስሀቅ በድሪ እንዲሁም የህክምና ቡድኑን አመሰግናለሁ።
ይመስገንልኝከልጅነት ዘመን ራሴን ሳውቅ ጀምሮ
ያሰቃየኝ ነበር ህመሙ የጆሮ
ከሀኪምቤት ሀኪምቤት እየቀያየርኩኝ
ከመርፌ ከክኒኒ ዝምድናን ፈጠርኩኝ
ህመም ሲበረታ ከልምድ ተነስቼ
ኪኒን እወስዳለሁ ከፋርማሲ አምጥቼ
የምውጠው ሁሉ እንኳንም ሊያድነኝ
ጨጓራዬን ልጦ ሌላ ህመም ሆነኝ
አንድ ቀን ጸጉር ቤት ልሰራ ስታጥበኝ
እሙ አደራ አልኳት ውሃ እንዳይገባብኝ
እሷም ከመቅስፈት ማጠቧን አቁማ
ምንሆነሽ ነው ብላ ጠየቀች ደጋግማ
ያመኛል ጆሮዬን እያልኩኝ ስነግራት
እምባዬን ሳወርደው ሆድ ብሶኝ ሳስረዳት
እኔ ምነግርሽን በደንብ አስተውይ
ቤተዛታ ሂጂ ሳታድሪ ሳትውይ
ዶ/ር ኢስሀቅ ሚባል ጎበዝ ሃኪም መጥቷል
የኔን መከራዬን ታሪኬን ቀይሯል
ከአንቺ የባስኩ እኔ በጣም የደፈነኝ
ከህመሜ ሁሉ እርሱ ገላገለኝ
ስላንተ ጥሩነት ችሎታህን ጭምር
በደስታ በኩራት ልጅት ስትናገር
በጣም ተገርሜ እኔም ተደስቼ
ከጸጉር ቤት ወጣው መሰራቴን ትቼ
ይሂስ እርግማን ነው የፈጣሪ ቁጣ
ብዬ አምኜ ነበር ዳንኩ የሚለኝ ሳጣ
እባክህ ጌታዬ ከንቱ ሆኝ አልቅር
መላ በለኝና የኔን ታሪክ ቀይር
እያልኩኝ ስጸልይ እሱን ሳስጨንቀው
የጸሎቴን ምላሽ ኢስሀቅን አገኘው
የውጭ ሀገር ገንዘብ ጥቅሙ ሳይበግርህ
እውቀቴን ላገሬ ለሀገሬ ብለህ
ካለህበት መጣህ ህሊና አስገድዶህ
የወገኔ ችግር ስቃዩ ሲታይህ
አንተ መልካም ብሩህ ዶ/ር
በጥቅማ ጥቅም የማትበገር
እኔም ተቀይሬ ከሰው እኩል ሆንኩኝ
ማማረሬን ትቼ ማመስገን ጀመርኩኝ
ይሄ ጅምርክ ነው መቼ ተነካና
ብዙ ሰው ሲሰማ እናያለን ገና
እረጅም እድሜ ይስጥህ ጤና
ሚጠብቅህ ብዙ አለና
ለጸሎቴ ምላሽ አምላክ የሰጠኝ
አንተን የፈጠረው ይመስገንልኝ
OUR STAFF PROMISES TO SERVE YOU

Address
- CMC Road Gurd Shola
Ethiopian Athletics federation building
3rd floor - otorhino@ethionet.et
P.O.Box 23282 Code 1000
Addis Ababa, Ethiopia
አድራሻ
- ሲ ኤም ሲ መንገድ ጉርድ ሾላ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ህንጻ
3ኛ ፎቅ otorhino@ethionet.et
P.O.Box 23282 Code 1000
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ



